ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በድሬ ደዋ ከተማ እየተካሄደ ባለው 3ኛ የፓን አፍሪካ የተማሪዎች እግር ኳስ ውድድር ሐረሪ ክልል ከምድቡ ማለፉን አረጋግጠዋል።
በውድድሩ አዲስ አበባ፣ድሬ ደዋ፣ኦሮሚያ፣ሀረሪ፣ሶማሌና አፋር በሁለት ምድብ ተደልለው ውድድራቸውን በድሬ ደዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ሐረሪ ክልልን በመወከል በውድድሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው አባድር 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እግር ኳስ ቡድን በኦሮሚያ 1ለ0 ተሸንፎ ከአዲስ አበባ ጋር ያለ ግብ 0ለ0 ተለያይቶ ኦሮሚያን በመከተል ከምድቡ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን ማረጋገጥ ችሏል።
እስካሁን አፋርና አዲስ አበባ ወደ ቀጣይ ዙር ሳያልፉ የቀሩ ሲሆን ኦሮሚያ፣ሐረሪ፣ሶማሌና ድሬ ደዋ በውድድሩ ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል።
ውድድሩ ነገ ቀጥሎ የሚደረግ ሲሆን ሐረሪ ክልል ከ ሶማሌ ክልል እንዲሁም ድሬ ደዋ ከ ኦሮሚያ ለፍፃሜ ለማለፍ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።






