በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙራድ አብዲም ውድድሩ ዘግይቶ የተጀመረ ቢሆንም በቀጣይነት የተበተኑትን የከተማችን ኮከቦች በማሰባሰብ ረገድ ካለው ጉልህ ሚና ባሻገር በአዲስ ፎርማት በሚደረገው ውድድር የእራሱን ብራንድ ይዞ የሚጓዝበት የእራሱ በመሣሪያ የተቀነባበረ ዜማ ጭምር እንደተዘጋጀለት ጠቅሰዋል።
በዚህ ውድድር አምና እና ካቻምና የታዩ የዲስፕሊን ጉድለቶችን ለመቅረፍ የውድድር ደንብ ቀርቦ የፀደቀ ሲሆን የውድድሩ ኮሚቴ መዋቀሩም ተገልጿል።
በቀጣይነትም ከክልል እግር ኳስ ሊግ ባሻገር የምስራቅ ዋንጫ በሚል በድሬዳዋ እና ሐረር ከተሞች መካከል ተጨማሪ የእግር ኳስ ፍልሚያ እንሚኖርም ተጠቅሷል።
በእለቱ በወጣው የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት መሰረትም የመክፈቻ መርሀ ግብሩ ሚያዝያ አስር ላይ በኢማም አህመድ ስቴድየም በሐረር ጀጎል እና የሐረር ሲቲ ቢ ቡድን መሐከል በሚደረግ ጨዋታ ይከወናል።




