የምስራቅ ኢትዮጵያ እግር ኳስ መሪዎች የተገኙበት የሐረሪ ሊግ በደመቀ ሁኔታ ተጀመረ

ለማጋራት

የሐረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የሐረሪ ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የሐረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የሶማሌ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የሐረሪ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። የሊጉ መጀመር በክልሉ ለሚገኙ ወጣት ስፖርተኞች ሰፊ የዕድገት ዕድል የሚፈጥር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም የጎረቤት ክልል ፌዴሬሽን መሪዎች በጋራ መገኘታቸው በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ያለውን ስፖርታዊ ወንድማማችነትና ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተመላክቷል።


ለማጋራት