Category: Football

የሀረሪ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በክልሉ ለሚገኙ የእግር ኳስ ፕሮጀክት አሰልጣኞች የእግር ኳስ ድጋፍ አደረገ

በዛሬው እለት የሀረሪ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በክልሉ ለሚገኙ 10 የU-13 የU-15 እና የ U-17 የእግር ኳስ ፕሮጀክት አሰልጣኞች የእግር ኳስ ድጋፍ አደረገ።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት አዲሱ የሀረሪ የእግር ኳስ ፌዴረሽን ፕረዚዳንት አቶ መሀመድ ያህያ እንደገለጹት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ፕሮጀክቱ ለወደፊቱ የክልሉ እግር ኳስ እድገት መሠረት በመሆናቸዉ መሠል ድጋፎችን በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በተጨማሪም ለታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት አሰልጣኞቹ የስራ አቅጣጫ ስጥተዋል ።

የምስራቅ ኢትዮጵያ እግር ኳስ መሪዎች የተገኙበት የሐረሪ ሊግ በደመቀ ሁኔታ ተጀመረ

የሐረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የሐረሪ ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የሐረሪ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የሶማሌ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የሐረሪ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። የሊጉ መጀመር በክልሉ ለሚገኙ ወጣት ስፖርተኞች ሰፊ የዕድገት ዕድል የሚፈጥር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም የጎረቤት ክልል ፌዴሬሽን መሪዎች በጋራ መገኘታቸው በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ያለውን ስፖርታዊ ወንድማማችነትና ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተመላክቷል።

የሐረሪ እግር ኳስ ሊግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት በዛሬው እለት ተካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙራድ አብዲም ውድድሩ ዘግይቶ የተጀመረ ቢሆንም በቀጣይነት የተበተኑትን የከተማችን ኮከቦች በማሰባሰብ ረገድ ካለው ጉልህ ሚና ባሻገር በአዲስ ፎርማት በሚደረገው ውድድር የእራሱን ብራንድ ይዞ የሚጓዝበት የእራሱ በመሣሪያ የተቀነባበረ ዜማ ጭምር እንደተዘጋጀለት ጠቅሰዋል።

በዚህ ውድድር አምና እና ካቻምና የታዩ የዲስፕሊን ጉድለቶችን ለመቅረፍ የውድድር ደንብ ቀርቦ የፀደቀ ሲሆን የውድድሩ ኮሚቴ መዋቀሩም ተገልጿል።

በቀጣይነትም ከክልል እግር ኳስ ሊግ ባሻገር የምስራቅ ዋንጫ በሚል በድሬዳዋ እና ሐረር ከተሞች መካከል ተጨማሪ የእግር ኳስ ፍልሚያ እንሚኖርም ተጠቅሷል።

በእለቱ በወጣው የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት መሰረትም የመክፈቻ መርሀ ግብሩ ሚያዝያ አስር ላይ በኢማም አህመድ ስቴድየም በሐረር ጀጎል እና የሐረር ሲቲ ቢ ቡድን መሐከል በሚደረግ ጨዋታ ይከወናል።

የተተኪ ስፖርተኞች ልማትን በማጠናከር የአሸናፊ አገር ለመገንባት ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለፁ

የተተኪ ስፖርተኞች ልማትን በማጠናከር የአሸናፊ አገርን ግብ ለማሳካትና ስኬቱን ለማስቀጠል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሚፈለገው መጠን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትና በተለየ አግባብ (Intervention)በመውሰድ የተተኪ ስፖርተኞች ልማት ስራን በተለይም በእግር ኳስ ስፖርት በአገሪቷ ያለውን የህዝቡን ፍላጎት እና ኢትዮጵያን የሚመጥን ውጤት በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ ለማስመዝገብ በህርሳቸው ተነሳሽነት (Initiative) ልዩ ስልት በመቀየስ ከመላ አገሪቱ በተወጣጡ ልዩ እምቅ አቅም (Talent)ያላቸውን ታዳጊዎች አሳታፊ በሆነ መንገድ በስፋት በመመልመል ልዩ ስልጠና በመስጠት አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መፍጠርን ያለመ ልዩ ፕሮግራም ነው፡፡

በዚህም መሰረት ልዩና ትልቅ አላማን ያነገበ ፕሮግራም ለማሳካት ያስችል ዘንድ በክልላችን ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ኦርዳን በድሪ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷት እየተመራ የሚገኝ ሲሆን በክልላችን ስር ተመዝግበው የሚገኙ ዕድሜያቸው ከ 15 ዓመት በታች የሆኑትን የታዳጊ ወጣቶች ቡድኖች መካከል ልዩ ተሰጦ ያላቸውን ለመመልመል ጥር 9/2018 ዓ/ም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በአሚር ሀቦባ ስቴዲየም በባለሞያዎች ምልመላው ይካሄዳል፡፡

በ3ኛ የፓን አፍሪካ የተማሪዎች እግር ኳስ ውድድር ሐረሪ ክልል ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን አረጋገጠ።

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በድሬ ደዋ ከተማ እየተካሄደ ባለው 3ኛ የፓን አፍሪካ የተማሪዎች እግር ኳስ ውድድር ሐረሪ ክልል ከምድቡ ማለፉን አረጋግጠዋል።

በውድድሩ አዲስ አበባ፣ድሬ ደዋ፣ኦሮሚያ፣ሀረሪ፣ሶማሌና አፋር በሁለት ምድብ ተደልለው ውድድራቸውን በድሬ ደዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ሐረሪ ክልልን በመወከል በውድድሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው አባድር 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እግር ኳስ ቡድን በኦሮሚያ 1ለ0 ተሸንፎ ከአዲስ አበባ ጋር ያለ ግብ 0ለ0 ተለያይቶ ኦሮሚያን በመከተል ከምድቡ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን ማረጋገጥ ችሏል።

እስካሁን አፋርና አዲስ አበባ ወደ ቀጣይ ዙር ሳያልፉ የቀሩ ሲሆን ኦሮሚያ፣ሐረሪ፣ሶማሌና ድሬ ደዋ በውድድሩ ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል።

ውድድሩ ነገ ቀጥሎ የሚደረግ ሲሆን ሐረሪ ክልል ከ ሶማሌ ክልል እንዲሁም ድሬ ደዋ ከ ኦሮሚያ ለፍፃሜ ለማለፍ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የ2017 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የክረምት በጎ አድራጎት የፖሊስ ሜዳ እግር ኳስ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ፡፡

በዕለቱም የጤና ቡድን እና የአዋቂዎች የአሸናፊዎች አሸናፊ የዋንጫ ጨዋታቸውን ያካሄዱ ሲሆን #በጤና የዋንጫ ጨዋታ የፖሊስ ሜዳ እግር ኳስ ቡድን CMSC እግር ኳስ ብድንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ቀጣይም #የአዋቂዎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዎታ የተካሄደ ሲሆን ቄራ እግር ኳስ ቡድን ቦቴ እግር ኳስ ቡድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን በዕለቱም ኮከቡ ተጫዋች በመሆን ተሸላሚ የሆኑት
ከጤና ቡድን #የፖሊስ ሜዳው ተጫዋች #ቢኒያም ሲሆን
ከአዋቂዎች የቄራው ተጫዋች #መሐመድ ሙስጠፋ የተዘጋጀውን ሽልማት መውሰድ ችለዋል ፡፡

የዋንጫ ባለቤት የሆኑት ቡድኖችም በዕለቱ በተገኙ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የተከበሩ አቶ ያሲን ዩሱፍ ፤ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሀብ እንዲሁም የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ፋትሒ አብዱሰመድ በጋራ በመሆን የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ማበርከት ችለዋል፡፡

የ2017 ዓ/ም የሐረሪ ክልል የክረምት በጎ አድራጎት የፖሊስ ሜዳ እግር ኳስ ውድድር የዋንጫ ተሸላሚ መሆን የቻሉ ቡድኖች፡፡

👉የአዋቂዋች የዙር አሸናፊ ቦቴ እግር ኳስ ብድን ዋንጫ እና የ50,000.00 ብር
👉የአዋቂዎች የጥሎ ማለፍ አሸናፊ ቄራ እግር ኳስ ብድን ዋንጫ እና የ30,000.00 ብር
👉የአዋቂዎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ቄራ እግር ኳስ ብድን ዋንጫ እና የ20,000.00 ብር
👉የጤና ቡድኖች አሸናፊ ፖሊስ ሜዳ እግር ኳስ ብድን ዋንጫ እና የ30,000.00 ብር
👉የታዳጊ ቡድኖች ሜንሽን እግር ኳስ ብድን ዋንጫ እና የ30,000.00 ብር ተሸላሚ መሆን ችለዋል፡፡